am_tn/lam/03/16.md

1.8 KiB
Raw Permalink Blame History

ጥርሴን በድንጋይ ሰበረ

ሊኖረው የሚችለው ትርጉም 1ድንጋይ እዲያኝክ ያደረገው እስኪመስለው ያህል እግዚአብሔር እንዳዋረደው። “አዋርዶኛል፤ ሌላን ሰው ድንጋይ እንዲበላ እንዳደረገ ሰው” ወይንም 2) ጸሓፊው እግዚአብሔር ፊቱን ከመሬት ጋር አጣብቆ እንዳዋረደው አድርጎ ነው የገለጸው። ““አዋርዶኛል፤ የሌላን ሰው ፊትን ከመሬት ጋር እንዳጣበቀ ሰው””

በትቢያ ውስጥ ረጋገጠኝ

ጸሓፊው እግዚአብሔር ወደ ትቢያ ውስጥ እንደገፋው እና እንዳዋረደው አድርጎ ይናገራል።

በትቢያ

ሊዋጋው የማይችለው ነገር ከመሆኑ የተነሳ እራሱን ሊያሳንስበት የሚችለው ትንሹ ደረጃ ለማለት ነው።

ነፍሴ ሰላምን አጣች

ሊኖረው የሚችለው ትርጉም 1የጸሓፊው ልምምድ ሰላማዊ አይደሉም “በሕይወቴ ሰላም የለኝም” ወይንም ጸሓፊው ሰላም አይሰማውም “በነፍሴ ሰላም አይሰማኝም”

ኋይሌ፤ ከእግዚአብሔርም ተስፋ ያደረግሁት ሁሉ ሄዶአል

ጸኋፊው መከራን መቋቋም ስለሚያስችለው ኋይሉ ይናገራል፤ ብሎም በእግዚአብሔር ላይ ስላለው ተስፋ ሊናገር ሕይወት እንዳላቸው እና አሁን እንደሞቱ ነገሮች አድርጎ ይናገራል። “ከዚህ በላይ መከራን መቀበል እና በእግዚአብሔር እንደሚረዳው ተስፋ ማድረግን እንዳቃተው”

ኃይሌ

አንዳንድ ቅጂዎች “ክብሬ” ወይንም “ተድላዬ”