am_tn/lam/03/05.md

2.6 KiB
Raw Permalink Blame History

ቅጥር ሠራብኝ

የቅጥር ሥራ የሚለው ቅጥር ያላቸው ከተማዎች ላይ ተንጠላጠሎ ለመውረር እንዲያስችላቸው የሚሰሩት ነው።

ቅጥር ሠራብኝ

ሊሆን የሚችሉት ትርጉሞች፤ 1ጸሓፊው እግዚአብሔር በከተማ ላይ መጣፎ ነገር ላማድረስ እንደሚቀጥር ክፋት እንዲደርስበት እንዳደረገ ይናገራል። “ጠላት በከተማ ላይ ጥቃትን ለማድረስ እንደ ሚቀጥርእግዚአብሔር አጠቃኝ” ወይንም 2ጸሓፊው እግዚኧብሔር ጠላት እየሩሳሌምን እንደሚወር እንደፈቀደ እግዚአብሔር አጠቃኝ ለማለት ነው። “ጠላት በዙሪያዬ ቅጥርን እንዲሰራ እግዚአብሔር አደረገ”

በምሬትና በድካም ዙሪያዬንም ከበበኝ

እግዚአብሔር ምሬትና ድካምን እዲለማመዱ ፈቅዷል። “ምሬትና ድካምን እድለማመድ አድርጓል” ወይንም “መከራን እና ብዙ ችግር እንዲደርስብኝ አድርጓል”

ምሬት

“ምሬት” የሚለው መከራን ያሳያል።

ከሞቱ ብዙ ጊዜ እንደሆናቸው፣ በጨለማ እንድኖር አደረገኝ።

“ጨለማ” የሚለው የሚናገረው ስለ መከራ ነው። ጸሓፊው የደረሰበትን መከራ መጠን ለመግለፅ ቀድሞ የሞቱ ሰዎች ከተለማመዱት ድቅድቅ ጨለማ ጋር ያወዳድረዋል። “እንዲደርስብኝ ያደረገው መከራ በመቃብር ውስጥ እንዳለ ጨለማ ነው” ወይንም “ ቀድማውንም የሞቱ ሰዎች ያሉበት ጨለማ ውስጥ ያለው ያህል እጅጉን መከራ ያደርስብኛል”

በቅጥር ውስጥ ዘጋብኝ፤ ስለዚህ ማምለጥ አልቻልሁም፤ የእስር ሰንሰለቴንም አከበደብኝ።

ይሄ ከእስር ቤት ማምለጥ እንዳቃተው ሰው ቀጣይነት ያለውን መከራ መቀበልን ያሳያል። ጸሓፊው መከራውን ማስቆም አልቻለም። “መከራዬ ቀጥሏል፤ በዙሪያዬ ቅጥርን የሰራ፣ ከባድ ሰንሰለትን ያደረገንኝ ያህል ነው፤ ማምለጥ ተስኖኛል”

ብጣራና ብጮኽ እንኳ . . . መስማት አልፈለገም

ጸሓፊው እግዚአብሔር ጸሎቱን ጆሮውን ደፍኖ አልሰማም እንዳለው ያህል እንደማይሰማው ይናገራል። “ጸሎቴን አልሰማም ይላል”