am_tn/lam/03/01.md

1.6 KiB
Raw Permalink Blame History

መከራ ያየ

“ያየ” ልምድ ያለውን ያሳል። “መከራን የተለማመደ” ወይንም “የተጎዳ”

በቊጣው በትር

“በትር ስር” የሚለው በበትር መመታትን ያሳያል። የእግዚአብሔርን ቅጣት በእርሱ በትር እንደመመታት ይተካዋል። “እግዚአብሔር እጅግ ስለተቆጣ በበትር መጥቶኛል” ወይንም “እግዚአብሔር እጅግ ስለተቆጣ በኋይል ቀጣኝ”

ከፊቱ አስወጣኝ

“ከእርሱ እንደሄድ አደረገኝ”

በብርሃን ሳይሆን በጨለማ እንድሄድ አደረገኝ

“ጨለማ” የሚለው የሚወክለው መከራን ነው። “በብርሃን ሳይሆ ን በጨለማ እንደሚሄድ ሰው ያለ ምንም ተስፋ እጅጉን እንድጎዳ አደረገ”

እጁን በላዬ ላይ መለሰ

“እጁን በላዬ ላይ መለሰ” የሚለው እርሱን ማጥቃትን ይወክላል። ጸሓፊው እግዚአብሔር መጠፎ ነገርን እንዲደርስበት መፍቀዱን እንዳጠቃው አድርጎ ይናገራል። “አጥቅቶኛል” ወይንም “ሰውን እንደሚያጠቃ ብዙ መጥፎ ነገሮች እንዲደርስብኝ አድርጎኛል”

ሥጋዬንና ቁርበቴን አስረጀ፥ አጥንቴን ሰበረ

ሊሆን የሚችሉት ትርጉሞች፤ 1ከመደብደብ የተነሳ የሚሆን ነገር ነው ወይንም 2እግዚአብሔር እርሱን የቀጣበት ሌላ መንገድ ነው።