am_tn/lam/02/21.md

1.9 KiB

ብላቴናውና ሽማግሌው በመንገዶች ላይ ተጋደሙ

እዚህ ጋር የሚናገረው ስለ ሞቱ ሰዎች እንደሆነ ያመላክትል። “የብላቴኖች እና ሽማግሌዎች ሬሳ በመንገዶች ላይ ተጋድሟል”

ብላቴናውና ሽማግሌው

ይሄ ክፍል የሚናገረው ስለ ሰዎች ነው። ሁለቱ ተቃራኒ የእድሜ ክልል የተጠቀሱት ሁሉንም ሰዎ ች ለመወከል ነው። “ወጣቱም ሽማግሌውም” ወይንም “በሁሉም የ ዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎች”

ደናግሎቼና ጐበዛዝቴ በሰይፍ ወድቀዋል

ሰይፍ የሚለው የሚወክለው ጠላቶቹን ነው። የተገደሉትም በጠላቶቻቸው ነው። “ደናግሎቼና ጐበዛዝቴ በጠላቶቻቸው ተገድለዋል”ወይንም “ጠላቶቼ ደናግሎቼን እና ጐበዛዝቴን ገድለዋቸዋል”

ገደልሃቸው

እግዚአብሔር እራሱ የገደላቸው ያህል ሰዎቹ እንዲገደሉ መፍቀዱን ይናገራል። “እንዲገደሉ ፈቀድክ” ወይንም “ይሄ እንዲፈጠር ፈቀድክ”

እንደ በዓል ቀን … ከዙሪያዬ ጠራህ

“ሊቡሉ እንደሚመጡ” ይቡሉ ዘንድ እንደሚመጠ እግዚአብሔር እንዴት ጠላቶቹን እንደጠራ።

የሚያስፈሩኝን

ጸሓፊው የሚፈራቸው ሰዎች “የሚያስፈራሩኝ” በሚል ተገልጿል። “የፈራኋቸው አጥቂዎቼ”

ከዙሪያዬ

ዘይቤአዊ አገላለጽ ነው። “በሁሉም አቅጣጫ”

በእግዚአብሔር ቍጣ ቀን

“ቀን” የሚለው በዘይቤአዊ አገላለጽ የተጻፈ ሲሆን የተወሰነ ግዜን የወክላል። “በእግዚአብሔር በቍጣው በተገለጠ ግዜ”