am_tn/lam/02/15.md

1.3 KiB

እጃቸውን … ያፍዋጫሉ ፥ ራሳቸውንም ያነቃንቃሉ

ሌሎችን ለመስደብ እና እነርሱ ላይ ለማሾፍ የሚደረጉ ድርጊቶች ናቸው። “እጃቸውን እያጨበጨቡ. . . እያፏጩ እና ራሳቸውንም ያነቃንቃሉ”

በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ

ይሄ ቅኔአዊ የእየሩሳሌም ስም ሲሆን ፣ እዚህ ጋር በሴት ይመስላታል።

በውኑ የውበት ፍጻሜና የምድር ሁሉ ደስታ የሚሉአት ከተማ ይህች ናትን?

ይሄ ምላሽ የማይጠብቀው ጥያቄ የፌዝ ንግግር ነው። ጥያቄ ባልሆነ መልኩ ሊጻፍ ይችላል። ““የውበት ፍጻሜ” እና “የምድር ሁሉ ደስታ” የተባለችው ከተማ ውበትም ድስታም የለባትም።

የውበት ፍጻሜ

በፍፁም ውብ

ጥርሳቸውን እያፋጩ

ይሄ የሰውን ቁጣ እና በሌላው ላይ ማፌዝን ነው የሚያሳየው።

ውጠናታል

እንስሳ ምግቡን እንደሚውጥ እየሩሳሌምን አጥፍተናታል። “እየሩሳሌምን ሙሉ ለሙሉ አጥፍተናታል”

አግኝተናታል አይተናትማል

ይህ ዘይቤአዊ አገላለጽ ነው። “ሲፈፀም ለማየት እጅግ ጓጉተን ነበር”