am_tn/lam/02/13.md

2.3 KiB

የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ?

እየሩሳሌምን ለመርዳት ምን ማድረግ እንዳለበት እንዳላወቀ ለማስታወቅ የሚጠይቀው ጥያቄ ነው እንጂ መልስ የሚጠይቅበት ጥያቄ አይደለም። ጥያቄ ባልሆነ መልኩ ሊጻፍም ይችላል፤ “ልለው የምችለው ነገር የለም. . . እየሩሳሌም”

የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ … ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ

ይሄ ቅኔ አዊ የእየሩሳሌም ስም ሲሆን ፣ እዚህ ጋር በሴት ይመስላታል። “ጽዮን” ሌላው የእስራኤል ስም ነው

በምንስ እመስልሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ

እየሩሳሌምን ለማጽናናት ምን ማድረግ እንዳለበት እንዳላወቀ ለማስታወቅ የሚጠይቀው ጥያቄ ነው እንጂ መልስ የሚጠይቅበት ጥያቄ አይደለም። ጥያቄ ባልሆነ መልኩ ሊጻፍም ይችላል፤ “ላወዳድርሽ የምችለው ነገር የለም. . . ጽዮን ሆይ”

ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነው

ባህር ታላቅ እንደ ሆነ የእየሩሳሌምም ስብራት እና ሰቆቃ እንዲሁ ነው። “ጉዳትሽ እንደ ባህር ታላቅ ነው”

የሚፈውስሽ ማን ነው?

“ማን ይፈውስሻል” ቀድሞ እንደነበረው ሊመልሳት የሚችል ማንም እንደ ሌለ ለመግለጽ የተጠቀመበት መንገድ ነው እንጂ መልስ የሚጠብቅ ጥያቄ አይደለም። በሌላ መልኩም ሊጻፍ ይችላል፤ “ማንም ሊፈውስሽ አይችልም” ወይንም “ማንም ሊመልስሽ አይችልም”

ምርኮሽንም ይመልሱ ዘንድ በደልሽን አልገለጡም

“ምርኮኛነትሽን ለማስቀረት፣ ኀጢአትሽን አይገልጡም”። “ምርኮሽን” ይሚለው የሰውን ሃብት እና ብልፅግና ያሳያል።

ከንቱና የማይረባ ነገርንም አይተውልሻል

አይተውልሻል የሚለው ”ተናግረዋል“ በሚለው ሊገለጽ ይችላል። “ከንቱና የማይረባ ነገርንም ተናግረውልሻል”