am_tn/lam/02/08.md

1.4 KiB

በጽዮን ሴት ልጅ ዙሪያ ያለውን ቅጥር፣ እግዚአብሔር ለማፍረስ ወሰነ

እግዚአብሔር የእየሩሳሌም ጠላቶች ቅጥሮቿን እንዲያፈርሱ መረጠ። እርሱ እራሱ ግን አላጠፋትም።

በጽዮን ሴት ልጅ

ይህ በቅኔአዊ አገላለፅ የእየሩሳሌምን ስም እንደ ሴት ሲመሰል ነው።

የመለኪያ ገመድ ዘረጋ

ከማጥፋቱ በፊት ቅጥሯን ምን ያህል እንደ ሚያፈርሰው ለማወቅ እንደሚለካ ሰው ይናገራል። “ቅጥሯን እንደለካ ሰው”

ከማጥፋትም እጆቹን አልሰበሰበም

ያለ ሁለት አሉታዊ አገላለፅ ለዘገብም ይችላል። ብሎም እግዚአብሔር የተመሰለው በእጆቹ ነው። “በእጆቹ ቅጥሮቿን አፍርሷል” ወይንም “ቅጥሮቿን አፍርሷል”

ምሽጎችና ቅጥሮች እንዲያለቅሱ አደረገ ፤ በአንድነትም ጠፉ

ምሽጎቿና ቅጥሮቿ በሰው ተመስለው፣ እንዳለቀሱ እና እንደሞቱ አድርጎ ይናገራል። “ምሽጎችና ቅጥሮቿን ስላጠፋ፤ አልቅሰው እንደደከሙ ሰዎች ሆነዋል“

ምሽጎች

ጥንታዊ ከተሞች ከአጥቂዎች የሚለይ ዋና “ቅጥር” ነበራቸው በውጪም በኩል ከ ቅጥሩ የሚከለክል ምሽግ።