am_tn/lam/02/05.md

2.0 KiB

ዋጠ

እግዚአብሔርን በሚባላ እንስሳ መስሎ ከተማይቷን ፈጽሞ እንዳጠፋት የሚያሳይበት መንገድ ነው።

አዳራሾችዋን … አምቦችዋን

እስራኤልን በሴት ይመስላታል

በይሁዳም ሴት ልጅ ኀዘንና ልቅሶ አበዛ

“ኀዘን”ና “ልቅሶ” የሚሉትን ቃላት በድርጊት መልኩ ሊገለፁ ይችላሉ። “የይሁዳ ሴት ልጆች ብዙ እንዲያዝኑ እና እንዲያለቅሱ ብዙ ብዙ አድርጓል።”

በይሁዳም ሴት ልጅ

ይሄ ቅኔአዊ በሴት የተመሰለ የእየሩሳሌም ስም ነው። “ይሁዳ”

ማደሪያውን እንደ አትክልት ስፍራ ባዶ አደረገ

ማደርያው እንደ አትክልት ሥፍራ በቀላሉ መነቀሉን ያሳያል። እግዚአብሔር የእስራኤል ጠላቶች እንዲያጠፉት ፈቀደ። እርሱ እራሱ አይደለም ያጠፋው። “ጠላቶቻቸው ማደሪያውን በቀላሉ እንደ አትክልት ሥፍራ እንዲጠፋ ያደረገው እርሱ ነው“

አትክልት ስፍራ

ትንሽ የአትክልት እና እርሻ ሥራ መስሪያ ዕቃዎች ማስቀመጫ ወይንም የሰራተኛው መጠለያ።

የበዓሉን ስፍራ አጠፋ

እግዚአብሔር የእስራኤል ጠላቶች እንዲያጠፉት ፈቀደ። እርሱ እራሱ አይደለም ያጠፋው። “የበዓሉን ስፍራ እንዲጠፋ ያደረገው እርሱ ነው” ወይንም “የእስራኤል ጠላቶች የበዓሉን ስፍራ እንዲያጠፉት ፈቀደ”

በጽዮን ዓመት በዓሉንና ሰንበቱን አስረሳ

በቀጠታ መልኩ መገለፅ ይችላል። “የጽዮን ሕዝብ በዓሉንና ሰንበቱን እንዲረሱ አደረጋቸው”

በጽኑ ቍጣው

“በእነርሱ ላይ እጅጉን ስለተቆጣ”