am_tn/lam/02/01.md

3.0 KiB
Raw Permalink Blame History

ጌታ በቍጣው የጽዮንን ሴት ልጅ እንደ ምን አደመናት

እግዚአብሔር ለእየሩሳሌም ያለውን ቁጣ በጥቁር ደመና ይመስለዋል። ሊኖሩት የሚችሉት ትርጉሞች፤ 1እግዚአብሔር በእየሩሳሌም ባሉ ሰዎች ላይ ጥፋትን እንደሚያመጣ እየዛተ ነው ወይንም 2እግዚአብሔር ሐዝቦቹ ላይ ጥፋትን አምጥቷል

የጽዮንን ሴት ልጅ … የይሁዳን ሴት ልጅ

እነኚህ ለእየሩሳሌም የተሰጡ ቅኔአዊ ስሞች ሲሆኑ፤ በሴትም መስሏቸዋል።

የእስራኤልን ውበት ከሰማይ ወደ ምድር ጣለ

“የእስራኤል ውበት” የሚለው እየሩሳሌምን ነው። በእስራኤል ያሉ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን እንዳጡ፤ እናም እርሱ ከመገኘቱ አውጥቶ እንደጣላቸው ይናገራል። “ከሰማይ ወደ ምድር” የሚለው የሚያሳየው በእግዚአብሔር ዘንድ ምን ያህል ሞገስን እንዳጡ ነው። “የእስራኤል ውበት የሆነችው እየሩሳሌም በእግዚአብሔር ፊት ሁሉንም ሞገስን አጥታለች” ወይንም “እየሩሳሌም ሁሉንም ሞገስዋን በእግዚአብሔር ፊት አጥታለች“

የእግሩን መረገጫ አላሰበም

ከዚህ በፊት እግዚአብሔር እየሩሳሌምን “የእግሩ መረገጫ” ብሏት እንደሚያውቅ ሲያመላክት፣ የሚወክለውም በእነርሱ ላይ የነበረውን ሥልጣን እና እነርሱም መገዛታቸውን ነው። እግዚአብሔር የእየሩሳሌምን የእግር መረገጫነት መርሳቱን እና መሻሩን ያመላክታል። “እየሩሳሌም የእግሩ መቀመጫ ከመሆን ሽሯታል።

አላሰበም

እግዚአብሔር እየሩሳሌምን የረሳት ያህል ችላ እንዳላት ያመላክታል። “ችላ ብሏታል” ወይንም “ትኩረት አልሰጣትም።

በቍጣውም ቀን

እዚህ ጋር ቀን የሚለው የተወሰነን የግዜ ክፍልን የሚያመላክትበት ዘይቤአዊ አገላለፅ ነው። “ቍጣውን በሚገልጽበት ግዜ . . . በቍጣውም ግዜ” ወይንም “ቁጣውን በሚያሳይበት ግዜ. . . በቁጣው ግዜ”

ዋጠ

እግዚአብሔርን በሚባላ እንስሳ መስሎ ከተማይቷን ፈጽሞ እንዳጠፋት የሚያሳይበት መንገድ ነው። “ፈጽሞ አጥፍቷት”

የያዕቆብን ማደሪያዎች ሁሉ

እዚህ ጋር “የያዕቆብ ማደሪያዎች” የሚለው በከተማው ይኖሩ የነበሩ የእርሱን ትውልዶች ያሳያል።

በመዓቱ የይሁዳን ሴት ልጅ አምቦች አፈረሰ

ሊኖረው የሚችለው ትርጉም 1በይሁዳ የፈራረሱ ከተሞች 2የፈራረሱ የእየሩሳሌም ቅጥሮ ች።