am_tn/jos/22/28.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

የሮቤል ነገድ፣ የጋድ እና የምናሴ ነገድ እኩሌታ አሁን መልሳቸውን ሰጥተው አበቁ፡፡

ይህ መነገር ካለበት… በእኛ እና በእናንተ መሃል ምስክሩ

ሶስቱ ነገዶች በቀረበባቸው ክስ በመጪው ዘመን ሊሆንም ላይሆንም ስለሚችለው ያላቸውን መልስ እየሰጡ ነው፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

አመጽ ከእኛ ይራቅ

የማመጽ ሃሳብ እንደሌላቸው ይህ ሃሳብ የተገለጸው፣ ከእነርሱ በጣም በሩቅ ስፍራ ላይ እንደሚገኝ ነገር ተደርጎ ነው፡፡ "እኛ በእርግጥ አናምጽም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱን ከመከተል ርቃችኋል

ያህዌን መከተልን ማቆም የተገለጸው እነርሱ ከእርሱ እንደዞሩ ተደርጎ ነው፡፡ "እርሱን መከተል አቆሙ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)