am_tn/jos/22/24.md

1003 B

አጠቃላይ መረጃ፡

የሮቤል ነገድ፣ የጋድ እና የምናሴ ነገድ እኩሌታ መልሳቸውን ሰጡ፡፡

የእናንተ ልጆች ለልጆቻችን እንዲህ ሊሉ ይችላሉ … ከእስራኤል አምላክ ጋር ምን አላችሁ?

ይህ ሶስቱ ነገዶች የሌሎች ነገዶች ልጆች ወደ ፊት ሊያደርጉት ይችላሉ ብለው ያሰቡት መላምታዊ ክስ ነው፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ከእስራኤል አምላክ ከያህዌ ጋር ምን አላችሁ?

ሶስቱ ነገዶች ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የተጠቀሙት ሊያስወግዱት የሚፈልጉትን ሁኔታ አጉልተው ለማሳየት ነው፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ከእስራኤል አምላክ ከያህዌ ጋር አንዳች የላችሁም!" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)