am_tn/jos/14/08.md

1.4 KiB

የህዝቡ ልብ በፍርሃት እንዲቀልጥ አደረጉ

ህዝቡ በጣም እንዲፈራ ማድረግ የተገለጸው የህዝቡ ልብ እንዲቀልጥ እንደተረገ ተደርጎ ነው፡፡ "ህዝቡ በጣም እንዲፈራ አደረጉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ ሙሉ ለሙሉ ያህዌን ተከተልኩ

ለያህዌ ታማኝ መሆን የተገለጸው ያህዌን ሙሉ ለሙሉ እንደ መከተል ተደርጎ ነው፡፡ "ሁሌም ለያህዌ ታማኝ ነበርኩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ምድሪቱ… ለአንተ እና ለልጆችህ ለዘለዓለም ርስት ትሆናለች

ካሌብ እና የእርሱ ትውልድ የሚኖራቸው ምድር የተገለጸው በቋሚነት እንደ ተቀበሉት ርስት ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያው አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)

እግርህ የረገጠውን ምድር

እዚህ ስፍራ "እግርህ" የሚለው የሚወክለው ካሌብን ነው፡፡ "የረገጥከው ምድር" (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልቱ)