am_tn/jos/11/10.md

1.7 KiB

ንጉሥዋን በሰይፍ መታ

"ኢያሱ የሐጾርን ንጉሥ በሰይፍ ገደለ"

ሐጾር የእነዚህ መንግሥታት ሁሉ ራስ ነበር

የሐጾር ከተማ ታላቅነት የተገለጸው ሐጾር የእነዚህ መንግሥታት ሁሉ ራስ ነበር በሚል ነው፡፡ "ሐጾር ከእነዚህ መንግሥታት ሁሉ ታላቅ ነበረች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያው አነጋገር እና ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚሉትን ይመልከቱ)

በዚያ የሚገኙትን ህይወት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ በሰይፍ መቱ… ስለዚህም በህይወት የተረፈ አንዳችም ህይወት ያለው ነገር አልነበረም

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ ሙሉ ለሙሉ ጥፋት መፈጸሙን ያጎላሉ፡፡(ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እንዲደመሰሱ እርሱ ለይቶ አስቀመጣቸው

"እርሱ" የሚለው ቃል ኢያሱን ያመለክታል፤ ደግሞም እርሱን ራሱን እና ሰራቱን ይወክላል፡፡ በከተማይቱ ውስጥ የሚገኙ ህይወት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ ሙሉ ለሙሉ መደምሰስ የሚለው የተነገረው እነዚያ ህይወት ያላቸው ነገሮች ሀሉ ለመጥፋት የተሰጡ እንደሆኑ ተደርጎ ነው፡፡ "ሰራዊቱ ሙሉ ለሙሉ ደመሰሳቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ እና ዘይቤያው አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)