am_tn/jos/08/15.md

2.2 KiB

ከእነርሱ አስቀድሞ ራሳቸው ይሸነፉ

"ከጋይ ሰዎች አስቀድሞ ራሳቸው ይሸነፉ" "ከእነርሱ አስቀድሞ" የሚለው ሃረግ የሚወክለው የጋይ ሶች የሚያዩትን እና የሚያስቡትን ነው፡፡ "የጋይ ሰዎች እስራኤላውያን እንደተሸነፉ ያስቡ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ከእነርሱ አስቀድሞ ራሳቸው ይሸነፉ

"ይሸነፉ" የሚለው ሃረግ በአድርጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የጋይ ሰዎች እስራኤላውያንን ያሸነፉ ይምሰላቸው" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ከእነርሱ አስቀድሞ… ተከትለው ሄዱ… እነርሱ ተባረሩ

እዚህ ስፍራ "ከእነርሱ" እና "እነርሱ" የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት የጋይን ሰራዊት ነው፡፡

እነርሱ ሸሹ … ከእነርሱ በኋላ ተከተሉ

እዚህ ስፍራ "ከእነርሱ" እና "እነርሱ" የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት የእስራኤልን ሰራዊት ነው

በከተማይቱ የነበሩ ሰዎች ሁሉ በአንድነት ተጠሩ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የከተማይቱ መሪዎች የከተማይቱን ህዝብ በአንድነት ጠሩ" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በከተማይቱ የነበሩ ሰዎች ሁሉ

ስለ ሁሉም ሰዎች አጠቃላይ በሆነ መንገድ ይጽፋል፣ ነገር ግን፣ "ሰዎች ሁሉ" የሚለው የሚያመለክተው መዋጋት የሚችሉትን ሰዎች ብቻ ነው፡፡ "በከተማይቱ የነበሩ የእስራኤልን ሰራዊት ማባረር የሚችሉ ሰዎች ሁሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና ማጠቃለያ የሚሉትን ይመልከቱ፡፡

ክፍት ትተው

"ከተማይቱን ክፍት ትተው"