am_tn/jos/08/01.md

1.6 KiB

አትፍሩ፣ ተስፋ አትቁረጡ

እነዚህ ሁለት ሃረጋት በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ያህዌ ያቀናጃቸው ለፍርሃት አንዳች ምክንያት ስለሌለ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የጋይን ንጉሥ… እና ምድሩን በእጆችህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ

እነርሱን ለእስራኤላውያን እጆች አሳልፎ መስጠት የሚወክለው ለእስራኤል ድልን እና የበላይነትን መስጠትን ነው፡፡ "በጋይ ንጉሥ እና በህዝቡ ላይ ደግሞም በእርሱ ከተማ እና በምድሩ ላይ ድልን ሰጥቼሃለሁ" (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ ሰጥቼሃለሁ

እግዚአብሔር ሊያደርግ ቃል የገባውን ልክ እንዳደረገው ያህል ይናገራል፣ ምክንያቱ እርሱ በእርግጥ ስለሚያደርገው ነው፡፡ "እኔ በእርግጥ ሰጥቼሃለሁ" ወይም "እኔ እሰጣለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትንቢታዊ ኃላፊ ጊዜ የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሷ ንጉሥ

"እርሷ" የሚለው ቃል የጋይን ከተማ ያመለክታል፡፡ ከተማዎች ብዙውን ጊዜ ሴት እንደሆኑ ተደርጎ ይነገሩ/ይገለጹ ነበር፡፡ "ንጉሥዋ" ወይም "የእነርሱ ንጉሥ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)