am_tn/jos/02/18.md

1.6 KiB

አያያዥ ሃሳብ፡

እስራኤላውያኑ ሰላዮች በኢያሱ 2፡15 የገለጹትን ሁኔታ ያብራራሉ፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡

እስራኤላውያኑ ሰላዮች ከረዓብ ጋር መነጋገራቸውን ቀጠሉ፡፡

ማናቸውም ከቤትሽ በር ውጭ የሄደ

ይህ ሃረግ መላምታዊ በመፍጠር አንድን ሁኔታ ይገልጻል፡፡ (መላምታዊ ሁኔታ የሚለውን ይመልከቱ)

ደሙ በራሳቸው ራስ ላይ ይሆናል

እዚህ ስፍራ "ደም" የሚለው የሚገልጸው የአንድ ሰውን መሞት ነው፡፡ ለራሳቸው ሞት ተጠያቂነቱ የተገለጸው ደም በራሳቸው ላይ እንደሚሆን ተደርጎ ነው፡፡ "ሞታቸው የገዛ ራሳቸው ጥፋት ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

እኛ በደለኞች አንሆንም

"ንጹሃን እንሆናለን"

በማንም ላይ እጅ ቢጫን

እዚህ ስፍራ "እጅ ቢጫን" የሚለው አንድ ሰው እንዲጎዳ ምክንያት መሆን በጨዋ አገላለጽ የተገለጸበት ነው፡፡ "በማንም ላይ ጉዳት እንዲደርስ ምክንያት ብንሆን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዩፊሚዝም/የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚለውን ይመልከቱ)