am_tn/jon/02/05.md

1.5 KiB
Raw Permalink Blame History

አጠቃላይ መግለጫ

ይህ በዮናስ 2፡2 የተጀመረው የዮናስ ጸሎት ተከታይ ክፍል ነው፡፡

ውኃዎቹ

‹‹ውኃዎቹ›› ባሕሩን ያመለክታሉ

አንገቴ

አንዳድ ትርጉሞችበዚህ ክፍል የተገለጸውን የዕብራውያኑን ቃል የሚረዱት ሕይወቴ›› በሚል ቃል ነው፡፡ በዚህ ትርጉም ውኃዎቹ የዮናስን ሕይወት ሊወስዱ ተቃርበው ነበር፡፡

ጥልቁ ሁሉ በዘዙራዬ ነበር

‹‹የጥልቁ ውኃ በዙሪያዬ ነበር››

የባሕር ሣር

በባሕር ውስጥ የሚበቅል ሣር

በምድርና በመወርወሪያዎችዋ ለዘላለም ተዘጋሁ

ዮናስ መሬትን እንደ እስር ቤት በምሳሌነት ተጠቀመ፡፡ መሬት እኔን ለዘላለም ለመዝጋት እንደ እስር ቤት ነበረች››

ነገር ግን አንተ ሕይወቴን ከጉድጓዱ ውስጥ አወጣሃት

ዮናስ የሞትን ሥፍራ ጉድጓድ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ነገር ግን አንተ ሕይወቴን ከሞት ሥፍራ አዳንሃት›› ወይም ነገር ግን አንተ ሕይወቴን ሙታን ከሚኖሩበት ሥፍራ አዳንሃት››

እግዚአብሔር አምላኬ!

በአንዳንድ ቋንቋዎች፣ ይህንን በአረፍተ ነገሩ መጀመሪያ ወይም ‹‹አንተ›› ከሚለው ቀጥሎ ማስቀመጡ የተለመደ ነው፡፡