am_tn/jon/02/03.md

1.2 KiB
Raw Permalink Blame History

አጠቃላይ መረጃ፡

ይህ በዮናስ 2፡2 የተጀመረው የዮናስ ጸሎት ተከታይ ክፍል ነው፡፡ በቁጥር 4 ዮናስ ከዚህ ጸሎት በፊት ስለ ጸለየው ጸሎት ይናገራል፡፡

ወደ ጥልቁ፣ ወደ ባሕሩ ልብ

ይህ ዮናስ የነበረበትን የባሕሩን ስፋት ያመለክታል፡፡

ወደ ባሕሩ ልብ ውስጥ

ወደ ባሕሩ ታችኛው ክፍል››

ፈሳሾችም በዙሪያዬ ነበሩ

‹‹የባሕሩ ውኃ በዙሪያዬ ከበበኝ››

ማዕበል እና ሞገዶች

እነዚህ በባሕሩ ታችኛ ክፍል ያሉ የሚረብሹ ነገሮች ናቸው፡፡

እኔም ተጣልሁ

ይህ እንደ ተግባር ሊገለጽ ይችላል፡፡ ‹‹አንተም አስወገድከኝ›› ወይም ‹‹ወደዚያ ላክኸኝ››

ከዓይኖችህ ፊት

እዚህ ላይ እግዚአብሔር የተገለጸው በ ‹‹ዓይኖቹ›› ነው፡፡ ከአንተ››

ነገር ግን ወደ መቅደስህ ደግሞ እመለከታለሁ

ዮናስ ከዚህ ሁሉ ከደረሰበት ባሻገር ፣ ቤተ መቅደሱን እንደሚያይ ተስፋ ያደርጋል፡፡