am_tn/jon/01/14.md

1.2 KiB
Raw Permalink Blame History

ስለዚህ

‹‹በዚህ ምክንያት›› ወይም ‹‹ባሕሩ እጅግ በመናወጡ ምክንያት››

ወደ እግዚአብሔር ጮሁ

‹‹ሰዎቹ ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ››

በዚህ ሰው ነፍስ ምክንያት አታጥፋን

‹‹ይህ ሰው እንዲሞት በማድረጋችን እባክህ አትግደለን›› ወይም ‹‹እኛ ይህ ሰው እንዲሞት ልናደርግ ነው፡፡ ነገር ግ እባክህ አትግደለን››

የዚህን ሰው ሞት በደል በእኛ ላይ አታድርግ

በእርሱ ሞት እኛን አትውቀሰን›› ወይም ‹‹ይህ ሰው ሲሞት እኛን እንደ በደለኛ አትቁጠረን፡፡›› ጸሐፊው ስለ ‹‹በደል›› በሰው ላይ እንደሚጫን ነገር አድርጎ ይናገራል፡፡ ይህም ያንን ሰው ተጠያቂ የሚያደርግ መሆኑን ያመለክታል፡፡

ባሕሩም ከመናወጡ ጸጥ አለ፡፡

‹‹ባሕሩ በአደገኛ ሁኔታ መንቀሳቀሱን አቆመ›› ወይም ‹‹ባሕሩ ተረጋጋ››

እግዚአብሔርን እጅግ ፈሩ

‹‹በእግዚአብሔር ኃይል እጅግ ተደነቁ››