am_tn/jon/01/04.md

1.6 KiB
Raw Permalink Blame History

ወዲያውም እንዲህ ሆነ

መርከቢቱም ልትሰበር ቀረበች በማለት ‹‹ሰዎቹ አሰቡ››

ልትሰበር ቀረበች

ይህ በድርጊታዊ አገላለጽ ሊቀርብ ይችላል፡፡ ‹‹ልትሰባበር’

መርከበኞቹ

በመርከቧ ላይ የሚሠሩ

የራሱን አምላክ

እዚህ ላይ ‹‹አምላክ›› የተባለው ሰዎች የሚያመልኳቸውን የስህተት አማልክትና ጣዖታት ለማመልከት ነው፡፡

በመርከቧ ውስጥ የነበረውን ዕቃ ወደ ባሕር ጣሉ

‹‹ሰዎቹ በመርከቧ ውስጥ የነበረውን ከባድ ነገር ወደ ብሕር ውስጥ ጣሉ፡፡›› ይህ የተደረገው መርከቧን ከመስጠም ለመጠበቅ ነው፡፡

ቀላል ለማድረግ

መርከቢቱ ቀላል ስትሆን በተሻለ ሁኔታ ትንሳፈፋለች፡፡ መርከቧ በተሻለ ሁኔታ እንድትሳፈፍ››

ነገር ግን ዮናስ ወደ መርከቧ ውስጠኛው ክፍል ውርዶ ነበር፡፡

ዮናስ ይህን ያደረገው ማዕበሉ ከመነሣቱ አስቀድሞ ነበር፡፡

ወደ መርከቧ ውስጠኛው ክፍል

‹‹ወደ መርከቧ ውስጥ››

በዚያ በከባድ እንቅልፍ ተኝቶ ነበር

‹‹በዚያ ከባድ እንቅልፍ ተኝቶ ነበር›› ወይም በዚያ ተኝቶ ነበር ከባድ እንቅልፍም ወስዶት ነበር፡፡›› ከዚህ የተነሳ ማዕበሉ ሊቀሰቅሰው አልቻለም፡፡