am_tn/jon/01/01.md

2.7 KiB
Raw Permalink Blame History

የእግዚአብሔር ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር መናገሩን የሚያመለክት አባባል ነው፡፡ ‹‹እግዚአሔር መልእክቱን ተናገረ››

የእግዚአብሔር ቃል

‹‹የእግዚአብሔር መልእክት››

ያሕዌ

ይህ በብሉይ ኪዳን ለሕዝቡ የገለጠላቸው የእግዚአብሔር ስም ነው፡፡ ይህንን ለመተርጎም ስለ ያሕዌ በትርጉም ቃል ገጽ ውስጥ የተሰጠውን ማብራሪያ ተመልከት፡፡

አማቴ

ይህ የዮናስ አባት ስም ነው፡፡ (ስሞችን ስለመተርጎም የሚለውን ተመልከት)

ተነሣና ወደ ታላቂቱ ከተማ፣ ወደ ነነዌ ሂድ

‹‹ወደ አስፈላጊዋ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ››

ተነሣና ሂድ

ይህ ወደ ሩቅ ሥፍራ ስለመሄድ የተለመደ አገላለጽ ነው፡፡

በእርስዋ ላይ ስበክ

እግዚአብሔር የሚያመለክተው የከተማዋን ሕዝቦች ነው፡፡ በእርስዋ ላይ ሕዝቡን አስጠንቅቃቸው››

ክፋታቸው ወደ ፊቴ ወጥቶአል

ያለማቋረጥ ኃጢአትን ያደርጉ እንደነበር አውቃለሁ፡፡

ከእግዚአብሔር ፊት ለመሸሽ ተነሣ

ከእግዚአብሔር ፊት መሸሽ›› ‹‹ተነሣ›› የሚለው የሚየመለክተው ዮናስ ከነበረበት ሥፍራ መሄዱን ነው፡፡

ከእግዚአብሔር ፊት

እዚህ እግዚአብሔር በሕልውናው ተገልፆአል፡፡

ወደ ተርሴስ ሂደ

ወደ ተርሴስም ሂደ፡፡›› ተርሴስ የምትገኘው ከነነዌ በተቃራኒ በኩል ነው፡፡ ይህ የበለጠ ግልጽ የሚሆነው ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ወደ ተርሴስ ይኮበልል ዘንድ ተነሣ በሚለው ላይ ነው፡፡

ወደ ኢዮጴም ወረደ

‹‹ዮናስ ወደ ኢዮጴ ሄደ››

መርከብ

‹‹መርከብ›› በባሕር ላይ ብዙ ተጓዦችን ወይም ከባድ ጭነት ተሸክሞ የሚጓዝ ትልቅ ጀልባ ነው፡፡

ዋጋ ከፈለ

‹‹ዮናስ ለጉዞው ከፈለ››

ወደ መርከቧ ገባ

በመርከቧላይ ወጣ››

ከእነርሱ ጋር

‹‹ከእነርሱ ጋር›› የሚለው ቃል በመርከቧ ውስጥ አብረው የሚጓዙትን ያመለክታል፡፡

ከእግዚአብሔር ፊት ኮበለለ

እዚህ ላይ እግዚአብሔር ሕልውናው ፊት በሚለው ቃል ተወክላል፡፡ ‹‹ከእግዚአብሔር ፊት ኮበለለ››