am_tn/job/39/19.md

32 lines
1.9 KiB
Markdown

# አያያዥ ሀሳብ፡
ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል
# አጠቃላይ መረጃ፡
እዚህ ስፍራ ያህዌ ሶስት ጥያቄዎች የጠየቀው ኢዮብ እንደ ያህዌ እንዳልሆነ ትኩረት ለመስጠት ነው፤ ምክንየቱም ኢዮብ የዱር/ያልተገራ ፈረስን ሊቆጣጠር አይችልም፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
# አንገቱን በጋማ ትሸፍናለህን?
ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "አንገቱን በጋማ ልትሸፍን አትችልም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
# አንገቱን በጋማ ልትሸፍን
የፈረስ "ጋማ" የተገለጸው የፈረስን አንገት እንደሚሸፍን ልብስ ተደርጎ ነው፡፡ "ጋማው አንገቱን እንደ ልብስ ይሸፍናል" (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
# በአንገቱ ላይ የወረደው ጋማ
በፈረሱ አንገት ላይ የሚገኘው ረጅም ፀጉር
# በእውኑ አንተ እንደ አንበጣ እንዲፈናጠር ልታደርገው ትችላለህን?
ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "አንተ እንደ አንበጣ እንዲዘል ልታደርገው አትችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
# ትልቅ አንበጣ
በጣም በፍጥነት እና በጣም ሩቅ ሊዘል የሚችል ትልቅ የአንበጣ አይነት
# ማሽካካት/ማንኮራፋት
ፈረሶች በአፍኝጫቸው የሚያወጡት በጣም ጉልህ ድምጽ