am_tn/job/38/19.md

3.5 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ሶስት ጥያቄዎችን የተጠቀመው እርሱ እንጂ ኢዮብ ብርሃንን እና ጨለማን እንደማይረዳ ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

አጠቃላይ መረጃ፡

እነዚህ ሁለቱ ሀረጎች እያንዳንዳቸው ሁለት ትይዩ ሀረጎች አላቸው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ብርሃን ማረፊያ ስፍራ ደግሞም ወደ ጨለማ የሚወስደው መንገድ የት ነው?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ወደ ብርሃን ወይም ወደ ጨለማ ስፍራ የሚወስደውን መንገድ አታውቅም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

የብርሃን ማረፊያ ስፍራ

"የብርሃን መኖሪያ፡፡" ብርሃን የተገለጸው ለእያንዳንዱ ቀን ተነስቶ የሚመጣበት ማረፊያ ስፍራ እንዳለው ተደርጎ ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ብርሃን

"የቀን ብርሃን" ወይም "የፀሐይ ብርሃን"

ብርሃንን እና ጨለማን ወደ ስራ ስፍራቸው ልትመራቸው ትችላለህን? ለእነርሱ ወደ ሆነው ቤታቸው መልሶ

የሚወስዳቸውን መንገድ ልታገኝ ትችላለህ? እነዚህ ጥያቄዎች አሉታዊ ምላሽ እንዲሰጥባቸው ይጠበቃል፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች በዐረፍተ ነገር መልክ ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ "ብርሃንን እና ጨለማን ወደ ስራ ስፍራቸው ልትመራቸው አትችልም ወይም ደግሞ የእነርሱ ወደ ሆነ ቤታቸው የሚመለሱበትን መንገድ ልታገኝ አትችልም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

ወደ ስራ ስፍራቸው

"ወደ አካባቢያቸው/መኖሪያቸው፡፡" ብርሃን እና ጨለማ የተነገሩት በእየዕለቱ የያህዌን ተግባር ለማከናወን እንደሚወጡና እንደሚገቡ ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ያለ ጥርጥር… እጅግ ትልቅ

ያህዌ ምፀታዊ ቀልድ የተጠቀመው ኢዮብ ብርሃንን እና ጨለማን እንደማይረዳ ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ "አንተ እንደማታውቅ ግልጽ ነው፣ ምክንያቱም እነርሱን ስፈጥራቸው አንተ ገና አልተወለድክም ነበር፣ ደግሞም አንተ በጣም አላረጀህም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)

በዚይን ጊዜ ተወልደህ እንደሆነ

"በዚያን ጊዜ አንተ ትኖር ነበር፡፡" "በዚያን ጊዜ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ብርሃን የተፈጠረበትን እና ከጨለማ የተለየበትን ጊዜ ነው፡፡ "እነርሱን በፈጠርኩበት ጊዜ አንተ ተወልደህ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

የቀኖችህ ቁጥር እጅግ ትልቅ ነው

"እጅግ ረጅም አመታት ኖረሃል"