am_tn/job/31/31.md

3.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ የእግዚአብሔር ቅጣት እንደማይገባው ሁኔታዎችን መግለጹን ቀጥሏል፣ ይልቁንም፣ ጥፋት እንደሌለበት እና ንጹህ እንደሆነ ያውቃል፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

የጎጆዬ/የቤቴ ሰዎች

ጎጆው የሚወክለው የኢዮብን ቤት ነው፡፡ የጎጆው ሰዎች የሚያጠቃልለው የቤተሰቡን አባላት እና አገልጋዮቹን ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ኢዮብን በሚገባ ያውቁታል፡፡ "የቤቴ ሰዎች" ወይም "የቤተሰቤ አባላት እና አገልጋዮቼ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ማን ከኢዮብ ገበታ ያልጠገበን ሰው ማግኘት ይችላል?

የኢዮብ ሰዎች ይህንን ጥያቄ ኢዮብ ለጋስ ሰው እንደሆነ በትኩረት ለመግለጽ ሊያነሱ ይችላሉ፡፡ "ሁሉም ከኢዮብ ገበታ በልቶ ጠግቧል!" ወይም "እኛ የምናውቀው ሁሉ የፈለገውን ያህል ከኢዮብ ምግብ ተመግቧል!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ባዕድ እንኳን በከተማ አደባባይ አይረሳም ነበር

ኢዮብ እንግዶችን እንዴት ይንከባከብ እንደነበር ተገልጽዋል፡፡ እዚህ ስፍራ "በከተማ አደባባይ መቀመጥ" የሚለው የሚገልጸው በከተማ አደባባይ ምሽቱን ማደርን ነው፡፡ "እንግዶች ፈጽሞውኑ በከተማይቱ አደባባይ በሜዳ ላይ አያድሩም ነበር" ወይም "እንግዶች/ባዕዳን ውጭ አያድሩም ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ሁሌም በሮቼን ለመንገደኞች ክፍት አደርግ ነበር

እዚህ ስፍራ "ለመንገደኞች በሬን እከፍት ነበር" የሚለው የሚወክለው ወደ ቤቱ መንገደኞችን መቀበሉን ነው፡፡ "ሁሌም መንገደኞችን በቤቴ እቀበል ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እናም ነገሩ ይህ ባይሆን፣ በዚያን ጊዜ በእኔ ላይ ክስ አቅርቡ

ይህ ሀረግ በመጀመሪያው ጽሁፉ በቀረበበት ቋንቋ ወይም በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ውስጥ የለም፡፡ እዚህ የተጨመረው በኢዮብ ረዘም ያለ ንግግር ውስጥ ያለውን ሀሳብ ላለማጉደል ነው፡፡