am_tn/job/31/11.md

2.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ የእግዚአብሔር ቅጣት እንደማይገባው ሁኔታዎችን መግለጹን ቀጥሏል፣ ይልቁንም፣ ጥፋት እንደሌለበት እና ንጹህ እንደሆነ ያውቃል፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ ክፉ ወንጀል በሆነብኝ ነበር

"ይህ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የኢዮብ ከሌላ ሴት ጋር የመተኛትን ክፉ በደል ነው፡፡

ይህ በዳኞች ቅጣት የሚያስጥል ወንጀል ይሆናል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ይህ ዳኞች በእኔ ላይ ቅጣት ቢጥሉ/ቢፈጽሙ ትክክለኛ ናቸው የሚያሰኝ ወንጀል ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ እሳት ያለውን ሁሉ ይፍጀው፣ አዝመራዬንም ከስሩ ጭምር ያቃጥለው

ኢዮብ ከሌላ ሰው ሚስት ጋር መተኛት የሚያስከትለውን ጥፋት እሳት ሁሉንም ነገር ከማጥፋቱ ጋር ያነጻጽረዋል፡፡ "ይህ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር መተኛትን ነው፡፡ "ማመንዘር ሁሉንም ነገር ከጫፍ ጫፍ እንደሚያጠፋ እና አዝመራን ሁሉ እንደሚያቃጥል እሳት ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከዳር እዳር ይፍጅ/ያቃጥል

እነዚህ ቃላት ምናልባት "ለቀሪው ዘመኔ አንዳች ሳያስቀር ሁሉንም ነገር ያጥፋ" ለሚለው ሀሳብ ዘይቤያዊ አገላለጽ ሊሆን ይችላል፡፡ ምናልባትም ደግሞ ይህንን ቃል በቃል መተረጎም ያስፈልጋል፡፡ ተከታዩን ይመልከቱ (፡en: ta: vol1: translate: figs:-metaphor)

አዝመራዬን ከስሩ ያቃጥል

እዚህ ስፍራ "ይህ" የሚለው ቃል ከሌላ ሰው ጋር የመተኛትን ድርጊት ያመለክታል፡፡ ይህ ድርጊት ኢዮብ ነገሩን አድርጎት ቢሆን ሊቀበለው ስለሚገባው ቅጣት በዘይቤ የቀረበ ነው፡፡ አዝመራውን የሚያቃጥል እሳት የደከመበትን ሁሉ ማጣት ለሚለው ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ/ ነው፡፡ "እኔን የሚቀጡ የደከምኩበትን ሁሉ ይውሰዱት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ተከታዩን ይመልከቱ (፡en: ta: vol2: translate: figs:-metonomy) እና(፡en: ta: vol2: translate: figs:-synecdoche)