am_tn/job/30/18.md

2.2 KiB

የእግዚአብሔር ታለቅ ሀይል በልብሴ አንቆ ይዞኛል

ኢዮብ፣ የእግዚአብሔር ሀይል አንዳች ነገር እያደረገ እንደሆነ እና እግዚአብሔር ሀይሉን እየተጠቀመ እንደሆነ ይናገራል፡፡ እዚህ ስፍራ "የእግዚአብሔር…ሀይል" የሚለው የቆመው/የሚገልጸው "እግዚአብሔርን" ነው፡፡ "እግዚአብሔር በታላቅ ሀይሉ በልብሴ አንቆ ይዞኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

መከራው እንደ ሸሚዜ ኮሌታ ዙሪያዬን አንቆታል

የእግዚአብሔር ሀይል በኢዮብ ዙሪያ መጠምጠሙ ዘይቤያዊ አነጋገር ነው፡፡ ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) የኢዮብን መከራ ይወክላል/ይገልጻል፡፡ "ስቃዬ እግዚአብሔር በሸሚዜ ኮሌታ አንቆ የያዘኝን ያህል ነው" ወይም 2) ይህ የሚገልጸው እግዚአብሔር በኢዮብ ላይ ብዙ መከራ እንዳደረሰበት ነው፡፡ "የሚሰማኝ እግዚአብሔር በታላቁ ሀይሉ በልብሴ አንቆ የያዘኝን ያህል ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ጭቃ ውስጥ ወረወረኝ

ኢዮብ እግዚአብሔር አዋርዶኛል እያለ ነው፡፡ "ያደረገኝ ልክ ጭቃ ውስጥ የመጣልን ያህል ነው" ወይም "እርሱ፣ ጭቃ ውስጥ የተጣለን ሰው ያህል አዋርዶኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ አዋራ እና አመድ ሆንኩ

ይህ የሚገልጸው ኢዮብ የተሰማውን እርባና ቢስነት ነው፡፡ "እንደ አብዋራ እና አመድ ጥቅም የማይሰጥ ሰው ሆንኩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)