am_tn/job/11/01.md

2.4 KiB

ነዕማታዊው ሶፋር

ይህ ስም በኢዮብ 2፡11 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ከነዕማታ ግዛት የሆነው ሶፋር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደዚህ የበዙ ጥያቄዎች/ቃላት መልስ ሊያገኙ አይገባምን?

ሶፋር ጥያቄውን በአሉታ የሚያቀርበው የኢዮብ ቃላት/ንግግር መገታት አለበት የሚለውን ለማጉላት ነው፡፡ "ለእነዚህ ንግግሮች ሁሉ እኛ መልስ ልንሰጥ ይገባል!" ወይም "አንድ ሰው ለዚህ ሁሉ ንግግር መልስ መስጠት ይኖርበታል!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ እንዲህ ንግግር የሚያበዛ ሰው ሊታመን ይገባዋልን?

ሶፋር ይህንን ጥያቄ የሚጠቀመው ኢዮብ የሚናገረውን ማመን እንደማይኖርባቸው ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "ይህ ሰው በንግግር የተሞላ ነው፣ ነገር ግን ሰዎች ሊያምኑት አይገባም!" ወይም "ብዙ ንግግርህ ብቻውን አንተ ንጹህ መሆንህን አያሳይም!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የአንተ መዘላበድ ሌሎች ዝም እንዲሉ ያደርጋልን?

ሶፋር ይህንን ጥያቄ የሚጠቀመው ኢዮብን ለመገሰጽ ነው፡፡ "አንተ ብዙ ስለተናገርክ ብቻ፣ ሌሎች ዝም ማለት አለባቸው ማለት አይደለም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ስትቀልድ፣ እንድታፍር የሚያደርግህ ሰው የለምን?

ሶፋር ይህንን ጥያቄ የሚጠቀመው ኢዮብን ለመገሰጽ ነው፡፡ ኢዮብ ቀለደ የተባለውን ይበልጥ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ "እኛ በተናገርነው ላይ አንተ ትቀልዳለህ/ታሾፋለህ፡፡ አሁን እኛ አንተን እናሳፍርሀለን!" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን እና (በ rc://*/ta/man/translate/figs-explicit ተመልከቱ)