am_tn/job/08/21.md

2.7 KiB

እርሱ ገና የአንተን አፍ በሳቅ፣ ከንፈሮችህን በእልልታ/በደስታ ጩኸት ይሞላዋል

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው ኢዮብ ትሁት መሆን ቢችል እንደምን ተመልሶ ደስተኛ ሊሆን እንደሚችል ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ "እርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ሲሆን "የአንተ" ሚለው ኢዮብን ያመለክታል፡፡ "ንጹህ ብትሆን እግዚአብሔር ዳግም በጣም ደስተኛ ያደርግሃል" (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

አፍህን በሳቅ ይሞላል

እግዚአብሔር ኢዮብን በሳቅ እንዲሞላ ደርጋል የሚለው ሀሳብ የተገለጸው እግዚአብሔር በኢዮብ አፍ ሳቅ እንደሚጨምር ተደርጎ ነው፡፡ "ሳታቋርጥ እንድትስቅ ያደርጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከንፈሮችህን በእልልታ/በደስታ ጨኸት

"ይሞላል" የሚለው ግስ በውስጠ ታዋቂነት በቀደመው ሀረግ ውስጥ ይገኛል፡፡ እግዚአብሔር የደስታ ጩኸት/ እልልታ እንዲያሰማ ማድረጉ የተገለጸው እግዚአብሔር በኢዮብ አፍ ደስታን እንደሚጨምር ተደርጎ ነው፡፡ "እግዚአብሔር በደስታ እንድትጮህ/እልል እንድትል ያደርጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተዘለለ/የተተወ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

አንተን የሚጠሉ ሀፍረት ይለብሳሉ

እዚህ "ሀፍረት" የሚለው ቃል የተገለጸው እግዚአብሔር የኢዮብ ጠላቶች እንዲለብሱት እንደሚያደርገው ልብስ ተደርጎ ነው፡፡ ይህ ማለት እነርሱ በጣም ያፍራሉ ማለት ነው፡፡ "እግዚአብሔር አንተን የሚጠሉትን በጣም እንዲያፍሩ ያደርጋቸዋል" (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከእንግዲህ የክፉዎች ድንኳን አይገኝም

እዚህ "ድንኳን" የሚያመለክተው የክፉዎችን ቤት ነው፡፡ "የክፉዎች ቤት ይደመሰሳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ከእንግዲህ አይገኝም

"አይቀጥልም" ወይም "ይደመሰሳል"