am_tn/jer/50/25.md

1.5 KiB

እግዚአብሔር ዕቃ ቤቱን ከፍቶ የቍጣውን ዕቃ ጦር አውጥቶአል።

የእግዚአብሄርን ቁጣ በባቢሎን ላይ ጠላቶቿን ላከ፡፡እግዚአብሄር ልክ የጦር እቃ እንዳለው መስሎ ይናገራል፡፡ “አውጥቶአል” የሚለው ቃል ለጦርነት መዘጋጀትን ያመለክታል፡፡

እቃ ቤቱን

ለጦርነት የሚያገለግሉ የጦር እቃ የሚቀመጡበት ክፍል ነው

በእርሱዋ ላይ ውጡ

እግዚአብሄር ለባቢሎን ጠላቶች ተናገረ፡፡ “የባቢሎን ጠላት ሆይ በእርሱዋ ላይ ውጡ”

ጎተራዎችዋንም ክፈቱ

ይህ የሚያመለክተው በባቢሎንን የተቀመጠ ሀብትን ነው፡፡ “ሀብቷ የተከማቸበትን ቦታ አጥቁአት”

ጎተራ

እህል የሚከማችበት ስፍራ

እንደ ክምርም አድርጓት

ይህ የሚያመለክተው 1) ከተማዋን እንደ ፕላስቲክ ክምር አርጎ መቀነስ 2) ከተማዋ ያላትን ሀብት ልክ እንደ እህል ክምር መከመር

አጥፉአት

ይህ የሚያመለክተው ሙሉ በሙሉ አጥፉአት ማለት ነው፡፡ኤርምያስ 25፡9 እንዴት እንደተረጎመው ተመልከት

አንዳችም አታስቀሩላት

ሙሉ በሙሉ አጥፉ የሚለውን አግንኖ የሚያሳይ ነው፡፡ “ሁሉንም በውስጧ ያሉትን ሰዎች አጥፉ”