am_tn/jer/50/11.md

2.0 KiB

አጠቃላይ ማብራሪያ

እግዚአብሄር ለባቢሎን ተናገረ

ደስ ብሎአችኃልና ሀሴትንም አድርጋችኋልና

እነዚህ ቃላቶች እስራኤልን በማሸነፋቸው ምን ያህል ደስ እንደተሰኙ አግንኖ የሚያሳዩ ናቸው፡፡

ደስ ብሎአችኋልና…በመስክ ላይም እንዳለች ጊደር ሆነችሁ…አሽካክታችኋልና

ከላይ ያሉት የባቢሎንን ህዝብ ያመለክታል፡፡

በመስክ ላይም እንዳለች ጊደር ሆነችሁ

የባቢሎን ህዝብ ደስታ ልክ በመስክ ላይ እንዳለች ጊደር ይመስለዋል፡፡

ተቀናጥታችኋልና

ይህ ጊደር መሬት በመርገጥ የምተሳየው ድርጊት ነው፡፡

እንደ ብርቱዎችም ፈረሶች አሽካክተችኋልና

የባቢሎን ህዝቦች ልክ እንደ ደስተኛ ፈረሶች ከፍ ያለ ድምፅ እንዳሰሙ አርጎ ይመስላቸዋል፡፡

እናታችሁ እጅግ ታፍራለች የወለደቻችሁም ትጎሳቆላለች

ይህ ሀረግ እፍረቷን አግንኖ የሚያሳይ ሲሆን “እናታችሁ” እና “የወለደቻችሁም” ባቢሎናውያንን ወይም የባቢሎን ከተማን ያመለክታል፡፡

በአህዛብ መካከል ኋለኛይቱ

የማትፈለገዋ ከተማ

ምድረበዳና ደረቅ ምድር በረሀም

እነዚህ ቃሎች የአንድ ምድርን ባዶነት አግንኖ የሚያሳይ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ ትርጉማቸው 1) ለኑሮ ምቹ ያለሆነ ቦታን ሲያሳይ 2) ባቢሎን ወደ በረሃነት እና ባዶነት አየሆነች መሆኑን ያሳያል

ባድማ ትሆናለች

ትጠፋለች

ይደነቃል

በፍራቻ ይንቀጠቀጣሉ

ያፍዋጫል

እባብ የሚያወጣውን አይነት ድምፅ ሲሆን ትልቅ ውድቀትን ያመለክታል