am_tn/jer/48/30.md

2.2 KiB

ይላል እግዚአብሄር

እግዚአብሄር ራሱን በስሙ የገለጸበት ምክንያት ቃሉን አስረግጦ ለመናገር ስለፈለገ ነው፡፡፤ ኤርምያስ 1፡8 የተተረጎመበትን መንገድ ይመልከቱ፡፡ ‹‹እግዚአብሄር የተናገረው ይህንን ነው›› ወይም ‹‹እኔ እግዚአብሄር የተናገርኩት ይህንን ነው››

እልኸኝነታቸውን አውቃለሁ

ይህ አረፍተነገር እግዚአብሄር የሞአብን እልኸኝነት የሚያሳይ ነው፡፡

እልኸኝነታቸው… ትምክህታቸው

እነዚህ የሚያመለክቱት የሞአብ ከተማ ህዝቦችን ነው፡፡

እልኸኝነታቸው

“ትእቢታቸው” ወይም “የትእቢትን ቃላት ተናገሩ”

ስለዚህ ለሞዓብ አለቅሳለሁ ለሞዓብም ሁሉ እጮኻለሁ

ሁለቱም አረፍተ ነገሮች አንድን ሃሳብ ይጋራሉ፡፡ “ለሞአብ ህዝቦች አለቅሳለሁ እጮኻለሁ”

አለቅሳለሁ

ይህ የሚያመለክተው 1) ኤርምያስን ያመለክታል 2) እግዚአብሄርን ያመለክታል

አለቅሳለሁ

በከፍተኛ ድምፅ እና ረጅም የሆነ ለቅሶ ሲሆን ምን ያህል እንዳዘነ ያሳያል

ቂርሔሬስ

ይህ የሞአብ የድሮ ዋና ከተማ ስም ነው፡፡

ኢያዜር … ሴባማ

እነዚህ የሞአብ ከተማ ስሞች ናቸው፡፡

አንቺ የሴባማ ወይን ሆይ…ቅርንጫፎችሽ ባህርን ተሻግረዋል… ወይንሽ

ሴባማ የምትባለው ከተማ ብዙ የወይን እርሻ አላት፡፡ እዚህ እግዚአብሄር ለሴባማ ህዝብን እንደ ወይን መስሎ ይናገራል፡፡ “የሴባማ ህዝብ ሆይ…”

አጥፊው በሰብልሽና በወይንሽ ላይ መጥቶአል፡፡

እግዚአብሄር የሴባማ ህዝቦችን እንደ ወይን መስሎ ይናገራል፡፡ “አጥፊው በሰብልሽ እና በወይንሽ ላይ መጥቶ ወስዶብሻል”

አጥፊው

የጠላት ስራዊት