am_tn/jer/48/26.md

2.3 KiB

በእግዚአብሔር ላይ ኰርቶአልና አስክሩት

እግዚአብሄር እየተናገረ ነው፡፡ “አስክሩት” የሚለው ትእዛዝ እግዚአብሄር ሊያመጣ ያለውን ነገር ያሳያል፡፡ በዚህ ላይ ሞአብን የሚያመለክት ሲሆን ሞአብ ሲል ደግሞ የሞአብ ህዝብን ያመለክታል፡፡ “እኔ እግዚአብሄር የሞአብ ህዝቦችን አሰክራለሁ በኔ ላይ ኮርተዋል እና”

አስክሩት

የእግዚአብሄር ቅጣት እንደ ወይን ስካር ሲመስለው የሚያረጉት ሁሉ በሞኝነት ስለሚሆን ሰዎች ይስቁባቸዋል፡፡ “እንደ ሰከረ ሰው አደርጋችኋለሁ”

ሞአብም በጥፋቱ ላይ ይነከባለላል..መሳቂያ ይሆናል

አሁንም እግዚአብሄር የሞአብ ህዝብን እንደ ሰከረ ሰው ይመስላቸዋል፡፡ “የሞአብ ህዝቦች በትፋቱ ላይ እንደሚንከባለል ይሆናሉ... መሳቂያም ይሆናሉ”

መሳቂያም ይሆናል

“ሰዎች ይስቁበታል”

እስራኤል ለአንተ መሳቂያ አልሆነምን?

ይህን ጥያቄ እግዚአብሄር ለሞአብ ህዝብ እስራኤላውያንን እንዴት ጨቆኑ ለማስታወስ ሲጠቀም ያሳያል፡፡ “በእስራኤል ህዝብ ላይ ስትስቁ ነበር”

እስራኤል…ተገኝቶአልን…አልሆነምን…ስለ እርሱ

“እስራኤል” የሚለው የእስራኤል ህዝብን ያመለክታል፡፡ “የእስራኤል ህዝብ…ተገኝተዋል…አልሆኑምን…ስለ እነርሱ”

በሌቦች መካከል ተገኝቶአልን? ስለ እርሱ በተናገርህ ጊዜ ራስህን ትነቀንቃለህ

ይህ ጥያቄ እግዚአብሄር የሞአብ ህቦችን በእስራኤላውያን ላይ ምንም ሳያረጉ እንዳሳፈሩአቸው ለመገሰፅ ይጠቀማል፡፡ “ምንም ሌቦች ባይሆኑም እንኳን ስለ እርሱ ራስህን ትነቀንቃለህ”

እርሱ በተናገርህ ጊዜ ራስህን ትነቀንቃለህ

ይህ አንድን ሰው ደስ በማይል አይን በመመልከት የምናሳየው ስሜት፡፡