am_tn/jer/48/08.md

1.8 KiB

አጥፊ ወደ ከተማ ሁሉ ይመጣል

“አጥፊ” የሚለው የሚያመለክተው የጠላትን ሰራዊት ነው፡፡ “የጠላት ሰራዊት ወደ ከተማ ሁሉ ይመጣል እርሱም ያጠፋቸዋል፡፡”

አንዲትም ከተማ አትድንም

“ከተማ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ቃል ህዝቡን ነው፡፡ “ማንም ህዝብ አይድንም፡፡”

ሸለቆውም ይጠፋል ሜዳውም ይበላሻል፡፡

“ሜዳው” እና “ሸለቆው” የሚሉት ቃላት ከተማዋን እና በዛ ስፍራ ያሉ ህዝቦችን ያመለክታሉ፡፡ “የጠላት ሰራዊት በሸለቆም ሆነ በሜዳ ላይ ያሉትን ሁሉ ያጠፋሉ”

በርራ እንድትወጣ ለሞአብ ክንፍ ስጡአት

ህዝቡን መርዳት እንደ ክንፍ ተሰጥቶአቸው ህዝቡ እንዲበር መስሎ ይናገራል፡፡ “እንደ ክንፍ ሰጥታችሁአቸው እንዲበሩ ያህል በሞአብ ያሉ ህዝቦችን እንዲሸሹ እርዱአቸው”

በርራ እንድትወጣ ለሞአብ ክንፍ ስጡአት

የዚህ የዋናው ቋንቋ ትርጉም ግልፅ አደለም፡፡ አንዳንድ የመፅሀፍ ቅዱስ ትርጉም “ለሞአብ ህዝብ መቃብርን አዘጋጁ የጠላት ሰራዊት ስለሚያጠፉአቸው” ይላሉ አንዳንዶች ደግሞ “በሞአብ ላይ ጨው ጨምሩ የጠላት ሰራዊት ያጠፉአቸዋልና” ጠላቶቻቸው ያጠፉአቸው ጊዜ መልሰው በዛ ስፍራ እንዳይኖሩ ይናገራሉ፡፡

ከደም የሚከለክል

“ደም” የሰውን ሕይወት ያመለክታል፡፡ “የሚከለክል” መግለደልን ያመለክታል፡፡”ሰውን የሚገድል”