am_tn/jer/48/01.md

1.9 KiB

አጠቃላይ ሀሳብ

ኤርምያስ በብዛት ትንቢትን በግጥም መልክ ይፅፋል፡፡ የእብረዊያን ፀሀፊዎች የተለያዩ ንፅፅር ይጠቀሙ ነበር፡፡

ሞአብ

ሞአብ ሕዝቡን ያመለክታለ፡፡ “ለሞአብ ህዝቦች”

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር

ኤርምያስ ማስተዋል ያለብንን መልእክት ሲያስተላልፍ የሚጠቀመው ሀረግ ነው፡፡ ኤርምያስ 6፡6 እንዴት እንደተረጎመው ተመልከት

ናባው ጠፍታለችና ወዮላት

ናባው ሕዝቡን ያመለክታል፡፡ “በናባው ያሉ ህዝቦች ጠፍተዋል እና ወዮውላቸው”

ናባው

በሞአብ ናባው ተራራ አካባቢ የሚገኝ ከተማ ነች፡፡

ቂርያታይም አፍራለች

“ቂርያታይም አፍራለች” የሚለው ህዝቡ ማፈሩን ይናገራል፡፡ “የቂርያታይም ከተመ በጠላት ከተማረኩ በኋላ ህዝቡን አሳፈሩአቸው”

ቂርያታይም

በሞአብ የምትገኝ ከተማ ነች፡፡

ብርቱ የሆኑ ምሽጎችዋም ይደመሰሳሉ ህዝብዋም በሀፍረት ላይ ይወድቃሉ

ይህ ህዝቡ በሀፍረት እንደወደቁ ያሳያል፡፡ “ጠላት የቂርያታይምን ብርቱ ምሽጎችን ይፈርሳሉ ህዝቦችዋም ያፍራሉ”

የሞአብ ትምክት የለም

ህዝቦች ሞአብን አይመኩባትም

ሐሴቦን

ይህ የከተማ ስምነው፡፡

ኑ ህዝብ እንዳትሆን እናጥፋ ብለው ክፉ ነገር አስበዋል፡፡

ይህ የሞአብ ህዝብን ያመለክታል፡፡

ሰይፍም ያሳድድሻል

“ሰይፍ” የጦር መሳሪያቸውን የያዙ ሰራዊትን ያመለክታል፡፡ “ጠላቶችህ ያሳድዱአችሁአል እናም ይገድሏቹሃል”