am_tn/jer/47/05.md

3.2 KiB

ቡሀነት በጋዛ ላይ መጥቶአል

ቡሀነት የሚለው መላጣን ያመለክታል፡፡ ጋዛ የሚለው ደግሞ ህዝቡን ያመለክታል፡፡ “የጋዛ ህዝቦች የራሳቸው ፀጉር ያልቃል”

ቡሀነት

እንደ ፊሊስጤም ከተማ ለጣኦት አምለኮ እና ለትልቅ ሀዘን ተብሎ የራስ ፀጉርን መላጨት፡፡

ዝም ትላለህ

ይህም ትርጉሙ 1) ህዝቡ ከሀዘን የተነሳ ዝም ይላሉ 2) የጠላት ሰራዊት ይገድላቸዋል፡፡

እስከ መቼ ድረስ ገላችሁን ትነጫላችሁ?

እግዚአብሄር ይህንን ጥያቄ የሚጠቀመው የአስቀሎ ህዝቦችን ማልቀስ እንደማያቆሙ ለማሳየት ነው፡፡ እግዚአብሄር ህዝቡን ሲናገር ለሴት እነደሚናገር አርጎ ነው የሚያሳየን፡፡ ይህችም ከተማዋን እነደሆነ ይናገራል፡፡

ገላችሁን ትነጫላችሁ

ቆዳን መቆራረጥ ሲሆን ጣኦትን ለማምለክ እና ለሞተ ሰው ለማልቀስ የሚደረግ ልምምድ ነው፡፡

በባህር ዳር ላይ ትዕዛዝ ሰጥቷል…

እዚህ ላይ ፍልስጤማውያን እየተናገሩ እንደሆነ ይመስላል፡፡ (ታሪካዊ መላምት የሚለውን ተመልከት)

አንተ የእግዚአብሔር ሰይፍ ሆይ፥ ዝም የማትለው እስከ መቼ ነው? ወደ ሰገባህ ግባ ጸጥ ብለህም ዕረፍ።

ፍልስጤማውያን የእግዚአብሄር ሰይፍ እንደሚሰማ መስለው ይናገራሉ፡፡ “እግዚአብሄር ሰይፍህን የያዝከው ምቼ ነው በሰይፍህ ዝም ማትለው”

የእግዚአብሄር ሰይፍ

እግዚአብሄር ፍልስጤማዋውያንን ሲቀጣ ከሰሜን የጦር ሰራዊትን ይልካል ይህም እግዚአብሄር ሰይፉን አንደዘረጋ መስሎ ይናገራል፡፡

ዝም የማትለው እስከ መቼ ነው?

የፍልስጤም ህዝቦች በጠላቶቻቸው በሚደርሰው ጥፋት ፍርሃታቸውን በዚህ ጥያቄ ይናገራል፡፡

ጸጥ ብለህም

ሰይፍ በቆራረጠ ቁጥር ድምፅ ያሰማል፡፡ የሰይፉን ድምፅ ፀጥ አሰኝ ሲል መገዳደሉን እና መቆራረጡን አስቁምልን ማለታቸው ነው፡፡ “አሳርፍ”

ሰገባህ

ሰይፍ መያዣ እቃ

እንዴት ዝም ትላለህ…በባህር ዳር ላይ

ኤርምያስ መናገሩን ቀጥሎአል፡፡ የእግዚአብሄር ሰይፍ አንደሚያርፍ መስሎ ይናገራል፡፡ እግዚአብሄር ፍልስጤምን ከሰሜን የጠላት ሰራዊትን በመላክ ቀጣቸው፡፡

እግዚአብሔር በአስቀሎናና በባሕር ዳር ላይ ትእዛዝ ሰጥቶአልና፥ በዚያም አዘጋጅቶታልና እንዴት ዝም ትላለህ?

ኤርምያስ ይህን ጥያቄ ሰይፉ ማቆም እንደማይችል አንዴ እግዚአብሄር አዞታልና መግደሉን እንደማያቆም ለማሳየት ይጠቀመዋል፡፡ “እግዚአብሄር አዞታል እና ማቆም አይችልም”