am_tn/jer/47/03.md

1.3 KiB

ከኃይለኞች ፈረሶች ከኮቴያቸው መጠብጠብ ድምፅ፥ ከሰረገሎቹም መሸከርከር፥ ከመንኰራኵሮቹም መትመም

የሚሰማው ድምፅ እየመጣ ያለ ሰራዊት እንዳለ ያመለክታል፡፡

ከሰረገሎቹም መሸከርከር፥ ከመንኰራኵሮቹም መትመም

እነዚህ ሁለቱ አንድን ነገር ሲገልፁ ይህም የሚናገረው በአንድላይ የሚያሰሙትን ከፍተኛ ድምፅ ለመግለፅ ነው፡፡

ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ያጠፋ ዘንድ የቀሩትንም ረዳቶች ሁሉ ከጢሮስና ከሲዶና ይቈርጥ ዘንድ ስለሚመጣው ቀን

ቀን የሚለው ተንቀሳቅሶ እንደሚደርስ መስሎ ይናገራል፡፡ “በዚያች ቀን የጠላት ሰራዊት ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ያጠፋል ከጢሮስ ይቆርጠዋል፡፡”

የቀሩትንም ረዳቶች ሁሉ ከጢሮስና ከሲዶና ይቈርጥ ዘንድ

አንድን ሰው ማስወገድ እነደ ቅርንጫፍ ከዛፍ ላይ እንደሚቆረጥ አርጎ ይመስለዋል፡፡ “ጢሮስና ከሲዶና የሚረዳ ሁሉ ይወገዳል”

ከፍቶርን

ከፍልስጤም በስተሰሜን የምትገኝ ዳርቻ ነው፡፡