am_tn/jer/47/01.md

1.6 KiB

ወደ ነብዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሄር ቃል ይህ ነው፡፡

ይህ ልዩ የእግዚአብሄር ቃል እንደሆነ ይናገራል፡፡ ኤርምያስ 14፡1 እንዴት እንደተረጎመው ተመልከት፡፡ “ይህ የእግዚአብሄር ቃል ለኤርምያስ የተሰጠ ነው”

የመጣው…ቃል ይህ ነው፡፡

ይህ የሚያመለክተው ከእግዚአብሄር ለየት ያለ መልእክት መናገር ሲፈልግ የሚጠቀመው ነው፡፡ “እግዚአብሄር ለኤርምያስ ይህን ቃል ሰጠው”

ፈርኦንም

“ፈርኦን” የሚለው ስም የግብፃውያንን ሠራዊት ያመለክታል፡፡ “የፈርኦን ሰራዊት”

እነሆ

“እነሆ” የሚለው ቃል ቀጣይ ለሚለው ነገር እንዲያስተውሉ ይናገራል፡፡

ውኃ ከሰሜን ይነሣል የሚያጥለቀልቅም ፈሳሽ ይሆናል

እነዚህ ሁለት ሀረጎች አንድ አይነት ሀሳብ የያዙ ሲሆን የጠላት ሰራዊት ደግሞ እንደ የሚያጥለቀልቅ ፈሳሽ መስሎ ይናገራል፡፡ “ከሰሜን ያለ ጠላት እነደ የሚያጥለቀልቅ ፈሰሽ ይመጣል”

በከተማይቱና በሚኖሩባት ላይ ይጐርፋል

ከሰሜን የሚመጣው ጠላት እንደ የሚጥለቀለቅ ፈሳሽ መስሎ ይናገራል፡፡ “አንደ ሚጥለቀለቅ ፈሳሽ ከሰሜን የሚመጣው ጠላት ከተማዋን ያጠፋታል”