am_tn/jer/46/25.md

1.6 KiB

የቴብስ አምላክ የሆነውን አሞንን

“አሞን” የግብፃውያን ጣኦት ንጉስ ነው፡፡ “ቴብስ” ከግብፅ በስተሰሜን የምትገኝ ከተማ ስትሆን ቴብስ የሚለው በቴብስ የሚገኙ ህዝቦችን ነው፡፡ “አሞን የቴብስ ጣኦት” ወይም “የቴብስ ህዝብ ጣኦት አሞን”

ግብፅንም አማልክተዋንና ነገስታቶችዋንም

ግብፅ የሚለው ህዝቡን ያመለክታል፡፡ “የግብፅ ህዝብ እና አማልክቶቻቸው”

ነፍሳቸውንም በሚፈልጉ ሰዎች እጅ…አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ

“እጅ” የሚለው ቃል ሀይል ወይም ጉልበትን ያመለክታል፡፡ “ነፍሳቸውንም በሚፈልጉ” ሲል ሰውን መግደል መፈለግ ማለት ነው፡፡ “እናንተን መግደል ለሚፈልጉ አሳልፌ እሰጣችሁአለሁ፡፡”

በባቢሎን ንጉስ በናቡከደነፆር እጅ በባሪያዎቹም

“እጅ” የሚለው ቃል ሀይል ወይም ጉልበትን ያመለክታል፡፡ “ናቡከደነፆር… ባሪያዎቹም” የሚለው “ነፍሳቸውን የሚፈልጉ” ያመለክታል፡፡ “የባቢሎን ንጉስ ናቡከደነፆር እና ባሪዎቹ ግብፃውያንን እንዲያሸንፉ አስልፌ እሰጣቸዋለሁ”

ከዚያም በኋላ አንደ ቀድሞው ዘመን የሰው መኖሪያ ትሆናለች

“ከዚህም በኋላ ሰዎች በግብፅ ከተማ መኖር ይጀምራሉ”