am_tn/jer/46/23.md

1.7 KiB

ይቈጠሩ ዘንድ የማይቻሉትን የዱርዋን ዛፎች ይቈርጣሉ… ይቈጠሩ ዘንድ የማይቻሉትን የዱርዋን ዛፎች ይቈርጣሉ

የግብፃውያን ጠላት ግብፅን በመውጋት እና መግደል ልክ እንደ ጠላት ሰራዊቱን እንደ እንጨት ቆራጭ መስሎ ይናገራል፡፡ “የጠላት ሰራዊት ግብፅን ይገድላል እንደ እንጨት ቆራጮች ዛፎችን እንደሚቆሩጡ”

ይላል እግዚአብሄር

እግዚአብሄር ራሱን በስሙ የገለጸበት ምክንያት ቃሉን አስረግጦ ለመናገር ስለፈለገ ነው፡፡፤ ኤርምያስ 1፡8 የተተረጎመበትን መንገድ ይመልከቱ፡፡ ‹‹እግዚአብሄር የተናገረው ይህንን ነው›› ወይም ‹‹እኔ እግዚአብሄር የተናገርኩት ይህንን ነው››

አንበጣ

ይህ የ ነፍሳት ዘር ሲሆን እጅግ በጣም ብዙ ሆነው የሚጓዙ እና በእህል ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚየሥከትሉ ናቸው፡፡

ቁጥርም የላቸውም

“ማንም ሊቆጥራቸው አይችልም”

የግብፅ ልጅ ታፍራለች

የግብፅ ህዝቦች አንደ የግብፅ ልጆች አድርጎ ይናገራል፡፡ “የጠላት ሰራዊት የግብፅ ህዝብን ያዋርዳል፡፡”

በሰሜን ሕዝብ እጅ አልፋ ትሰጣለች።

“እጅ” የሚለው ሀይል ወይም ጉልበትን ያመለክታል፡፡ “እኔ እግዚአብሄር ከሰሜን ያሉ ህዝቦች ግብፅን እንዲያሸንፉ አዛለሁ፡፡”