am_tn/jer/46/11.md

1.4 KiB

አጠቃላይ ሃሳብ

እግዚአብሄር ለግብፅ የሚናገረውን ጨረሰ

ወደ ገለዓድ ውጪ የሚቀባንም መድኃኒት ውሰጂ

ገለዓድ የሚባለው ስፍራ ታዋቂ የሆነ መድሃኒት የሚቀምሙ ሰዎች ያሉበት ስፍራ ሲሆን እግዚአብሄር መድሃኒት እንደማረዳቸው እያወቀ መድሃኒት ውሰዱ እያለ ይቀልድባቸዋል፡፡

ድንግሊቱ የግብፅ ልጅ ሆይ

የግብፅ ሀገር ህዝቦች እንደ ድንግል ልጅ መስሎ ይናገራል፡፡ “የግብፅ ህዝቦች”

ጉስቁልና

ይህ ክብር ማጣት ወይም የማፈር ስሜት ነው፡፡

ለቅሶሽም ምድርን ሞልቶአታል

“ምድርን” ሲል በምድር ላይ ያሉ ሰዎችን እና በግብፅ ላይ የደረሰውን የሚያውቁ ህዝቦችን ነው፡፡ የግብፃውያንን ለቅሶ የሚሰሙ ህዝቦች ሁሉ እንደ ለቅሶአቸው ምድርን እንደሞላ መስሎ ይናገራል፡፡ “በምድር ላይ ያሉ ህዝቦች ሁሉ ለቅሶሽን ይሰሙታል”

ኃያሉ በኃያሉ ላይ ተሰናክሎ ሁለቱ በአንድነት ወድቀዋልና

ሃያላን በጦርነት መሞታቸውን እንደ ተሰናክለው እንደወደቁ መስሎ ይናገራል፡፡ “የጦር ሰራዊታችሁ በጦርነት ይሞታሉ”