am_tn/jer/41/01.md

1.2 KiB

በሰባተኛውም ወር

በእብራውያን ቀን አቆጣጠር ሰባተኛው ወር ነው፡፡ ይህም እንደ ምዕራባውያን አቆጣጠር የሴፕቴምበር መጨረሻዎቹ ላይ እና ኦክቶበር መጀመሪያዎቹ ላይ ነው፡፡

የኤሊሳማ ልጅ የናታንያ

እነዚህን ስሞች በኤርምያስ 40፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎመው ተመልከት

እስማኤል

ይህ የሰው ስም ነው

የሳፋንን ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን

የእነዚህን ሰዎች ስም በኤርምያስ 39፡14 እንዴት እንደተረጎመው ተመልከት

በአገሩ ላይ የሾመውን

“በአገሩ” የሚለው ህዝቡን ያመለክታል፡፡ “በይሁዳ ህዝብ ላይ ሾመው”

እስማኤልም….ገደላቸው

“እስማኤል” የሚለው ቃል ራሱን እና ከእርሱ ጋር የነበሩትን አስር ሰዎችን ያመለክታል፡፡ “እስማኤል እና አስር ሰዎች…ገደሉአቸው”

በዚያም የተገኙትን የከለዳውያንን ሰልፈኞች

“በዛም ያሉትን የከለዳውያን ሰራዊቶችን”