am_tn/jer/32/41.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

ለእነርሱ መልካም ማድረግ

እዚህ ስፍራ "እነርሱ" የሚለው የሚያመለክተው እስራኤላውያንን ነው፡፡

እኔ እነርሱን በዚህች ምድር በታማኝነት እተክላቸዋለሁ

ያህዌ የእርሱ ህዝብ ህይወት በአትክልት ስፍራ እንደተከለው ተክል ለዘለአለም እንደሚኖር አድርጎ ይናገራል፡፡ "እኔ እስራኤላውያንን በቋሚነት በዚህ ምድር አስቀምጣቸዋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በሙሉ ልቤ እና በህይወቴ ሁሉ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች በአንድነት የአንድን ሰው ሁለንተና የሚያመለክት ፈሊጣዊ አገላለጽን ይሰጣሉ፡፡ "በፍጹም ማንነቴ" ወይም "በሙሉ ልቤ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

እኔ እነዚህን ሁሉ ታላላቅ ጥፋቶች በዚህ ህዝብ ላይ አምጥቻለሁ፣ እንደዚሁ ደግሞ መልካም ነገሮችን ሁሉ ለዚህ ህዝብ አደርጋለሁ

"እነዚህ ሁሉ መጥፎ ነገሮች በዚህ ህዝብ ላይ እንዲደርስ አድርጌያለሁ፣ አሁን ደግሞ መልካም ነገሮች እንዲሆንላቸው አደርጋለሁ"