am_tn/jer/32/36.md

1.4 KiB

እናንተ የተናገራችሁት

እዚህ ስፍራ "እናንተ" የሚለው ብዙ ቁጥር ነው፡፡ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ኤርምያስን እና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ይገልጻል፣ ወይም 2) ሁሉንም ሰዎች ያመለክታል፡፡ (አንተ/አንቺ የሚለውን ተውላጠ ስም መልኮች ይመልከቱ)

እርሷ ለባቢሎን ንጉሥ እጆች ተሰጠች

እዚህ ስፍራ "እጅ" ማለት ሀይል ወይም ቁጥጥር ማለት ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ያህዌ ለባቢሎን ንጉሥ እርሷን/ከተማይቱን እንዲገዛ ሀይል ሰጠው" (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

እነርሱን ለመሰብሰብ

"የእኔን ህዝብ ለመሰብሰብ"

ንዴት፣ መዓት፣ እና ታላቅ ቁጣ

ሶስቱም ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም ሲይዙ እርሱ ምን ያህል እንደተቆጣ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ "ከመጠን ያለፈ ቁጣ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

በደህንነት

"እነርሱ በሰላም ባሉበት"