am_tn/jer/32/16.md

2.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤርምያስ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ ረጅም ጸሎት ጀመረ፣ ከረጅም እንጉርጉሮ ጋር ምስጋና ጭምር አቀረበ፡፡

የግዢ ደረሰኝ

ይህ ማለት የታተመው ጥቅልል እና ያልታተመ ጥቅልል ነው

አወይ፣ ጌታ ያህዌ! እነሆ!

እዚህ ስፍራ "አወይ/ወየው" የሚለው ቃል በዚህ ጸሎት ኤርምያስ ማዘኑን፣ ማጉረምረሙን እና እንጉርጉሮ ማሰማቱን ያመለክታል፡፡ "እነሆ/እዩ" የሚለው ቃል ቀጣዮቹ ቃላት ለጸሎቱ በጣም አስፈላጊ የሆነ መግቢያ ወይም ዳራ መሆኑን ያመለክታል፡፡ (የመረጃ ዳራ የሚለውን ይመልከቱ)

በታላቅ ጥንካሬህ እና በተነሳው ክንድህ

"የተነሳ ክንድ" የሚለው ሀረግ ለክንድ ጥንካሬ ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፤ ስለዚህም "ታላቁ ጥንካሬህ" የሚሉት ቃላት እና "የተነሱት ክንዶችህ" የሚለው ጥንድ ትርጉምን ይሰጣል፡፡ "በታላቁ ሀይልህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ጥንድ ትርጉም የሚሉትን ይመልከቱ)

አንተ የቃል ኪዳን ታማኝነትን ለሺህዎች አሳይተሃል

"ታማኝነት" የሚለው ረቂቅ ስም "ታማኝ" ወይም "በታማኝነት" ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "አንተ ለሺህዎች ለቃል ኪዳንህ ታማኝ ነህ" ወይም "አንተ ቃል ኪዳንህን ትጠብቃለህ፣ ደግሞም ሺህዎችን በታማኝነት ትወዳለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

የሰዎችን ጥፋት ከእነርሱ በኋላ በሚመጡት ልጆቻቸው ጭን ላይ አፍስስ

"ጥፋት" የሚለው ቃል ያህዌ ህዝቡን ለመቅጣቱ ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፤ ምክንያቱም እነርሱ ክፉ ነገሮችን በማድረግ ጥፋተኞች ናቸው፡፡ የያህዌ ህዝቡን መቅጣት የተገለጸው ፈሳሽ በትልቅ ማጠራቀሚያ የሞላ ፈሳሽን እንዳፈሰሰባቸው ወይም በተቀመጡበት በጭናቸው ላይ ትንንሽ እቃዎችን እንደጣለባቸው ተደርጎ ተገልጽዋል፡፡ "አንተ ልጆችን በወላጆቻቸው ኃጢአት ምክንያት ትቀጣለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)