am_tn/jer/32/13.md

1.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤርምያስ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

በእነርሱ ፊት

እዚህ ስፍራ "እነርሱ" የሚለው የሚያመለክተው አናምኤልን፣ ምስክሮችን፣ እና በዚያ የነበሩ አይሁዳውያንን ነው፡፡

የሰራዊት ጌታ ያህዌ… እንዲህ ይላል

ኤርምያስ ብዙውን ጊዜ እነዚህን ቃላት የሚጠቀመው ከያህዌ ዘንድ ጠቃሚ መልዕክትን ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 6፡6 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

ቤቶች፣ እርሻዎች፣ እና የወይን ቦታዎች ዳግም በዚህ ስፍራ ይገዛሉ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "የእስራኤል ሰዎች ዳግም በዚህ ምድር ቤቶችን፣ የወይን ቦታዎችን እና እርሻዎችን ይገዛሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ እና ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)