am_tn/jer/32/10.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤርምያስ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

ጥቅልሉ ታትሞበት፣ ደግሞም ምስክሮች ምስክርነት ሰትተውበት

ይህ የሚያመለክተው አንድ ሰው መሬት ለመግዛት በሰነዱ ላይ የሚያደርገውን ፊርማ ነው፡፡ ኤርምያስ ይህንን መሬት መግዛን ለማረጋገጥ ሌሎች ሰዎች ምስክሮች ይሆናሉ፡፡

ምስክሮች ምስክር ይሆናሉ

"መሬቱን ስገዛ ሰዎች ተመልክተዋል፣ ስለዚህ እኔ መሬቱን ለመግዛቴ ለሌሎች መናገር ይችላሉ"

የታተመ ነበር

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እኔ እንዳተምኩት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ያልታተመበት ሰነድ

"ክፍት ቅጂ" ወይም "በላዩ ማህተም የሌለበት ሰነድ"

ባሮክ…ኔርያ…መሕሤያ

እነዚህ የወንድ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

የዘብ ጠባቂዎች አደባባይ

ይህ በግንብ የተከበበ እና እስረኞችን የሚጠብቁበት ከንጉሡ ቤተመንግስት ጋር የተያያዘ ክፍት ስፍራ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 32፡2 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡