am_tn/jer/32/01.md

1.9 KiB

ይህ ከያህዌ ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ነው

ይህ ፈሊጥ የዋለው እግዚአብሔር ለኤርምያስ መልዕክት እንደ ሰጠው ለማወጅ ነው፡፡ ተመሳሳይ የሆነው ሀረግ በኤርምያስ 1፡2 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ያህዌ ለኤርምያስ መልዕክት ሰጠው" ወይም "ያህዌ ኤርምያስን ተናገረው/እንዲህ አለው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሰ በአስረኛው አመት፣ በናቡከደነጾር አስራ ስምንተኛ አመት

"ሴዴቅያስ ለዘጠኝ አመታት የይሁዳ ንጉሥ ከሆነ በኋላ እና ናቡከደነጾር ከአስራ ሰባት አመታት በላይ ከነገሰ በኋላ"

ነቢዩ እርምያስ ታስሮ ነበር

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ኤርምያስን እስረኛ አድርገውት ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ነቢዩ እርምያስ ታስሮ ነበር

እዚህ ስፍራ ኤርምያስ ለምን ራሱን በስም እንደሚጠቅስ ግልጽ አይደለም፡፡ በዩዲቢ ውስጥ እንደሚገኘው የመጀመሪያ መደብ በመጠቀም መተርጎም ትችላላችሁ፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚሉትን ይመልከቱ)

በይሁዳ ንጉሥ ቤት የንጉሡ ዘብ ጠባቂዎች አደባባይ

ይህ በግንብ የተከበበ እና እስረኞችን የሚጠብቁበት/የሚያስሩበት ከንጉሡ ቤተመንግስት ጋር የተያያዘ ክፍት ስፍራ ነው፡፡