am_tn/jer/30/08.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ለእስራኤላውያን መናገሩን ቀጥሏል፡፡

የአንገታችሁን ቀንበር እሰብራለሁ፣ ደግሞም ሰንሰለታችሁን እበጥሳለሁ

ባሪያ መሆን የተገለጸው እንደ እንስሳ ቀንበር እንደ መጫን እና እንደ እስረኛ ሰንሰለት እንደመልበስ/በሰንሰለት እንደ መታሰር ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አምላካቸውን ያህዌን ያመልኩታል… ንጉሣቸው… በእነርሱ ላይ

ያህዌ ስለ ያዕቆብ ትውልድ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ "አምላካችሁን ያህዌን ታመልኩታላችሁ… ንጉሣችሁ… በእናነት ላይ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

ንጉሣቸው ዳዊት

ይህ ከዳዊት ትውልዶች ለአንዱ ሜቶኖሚ/ ነው፡፡ "ከንጉሣቸው ከዳዊት ትውልድ የሆነ " በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)