am_tn/jer/29/15.md

2.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤርምያስ ምርኮኛ ለሆኑ እስራኤላውያን መናገሩን ቀጥሏል

በዳዊት ዙፋን ላይ ሚቀመጠው ንጉሥ

በዙፋን ላይ መቀመጥ ንጉሥ ሆኖ መግዛት ለሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ነው፡፡ "እስራኤላውያንን ዳዊት ይገዛ እንደነበረው የሚገዛ ንጉሥ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል

ኤርምያስ ብዙውን ጊዜ እነዚህን ቃላት የሚጠቀመው ከያህዌ ዘንድ ጠቃሚ መልዕክትን ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 6፡6 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

እዩ

ይህ አንባቢውን ቀጥሎ ለሚሆነው ነገር ያነቃዋል፡፡ "ተመልከቱ" ወይም "አድምጡ" ወይም "ትኩረት ስጡ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

እኔ ሰይፍ፣ ረሃብ፣ እና ጥፋት በእነርሱ ላይ ልልክባቸው ነው

"ሰይፍ" የሚለው ቃል ለጦርነት ሜቶኖሚ/ነው፡፡ ሰይፍ፣ ረሃብ እና ጥፋት የተነገሩት እስራኤልን ለመጉዳት ያህዌን እንደሚታዘዙ ሰዎች ተደርገው ነው፡፡ "እኔ በጦርነት፣ በረሃብ፣ እና በበሽታ እንዲሞቱ ልቀጣቸው ተነስቻለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ሰውኛ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ለመበላት እንደማይችል እጅግ እንደ ተበላሸ በለስ አደርጋቸዋለሁ

የተበላሸ በለስ ጥቅም የለውም ምክንያቱም ሊበላ አይችልም፣ እንደዚያው ያህዌ የእስራኤልን ህዝብ ምንም የማይጠቅም አድርጎ አይቶታል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)