am_tn/jer/28/10.md

1.7 KiB

ልክ እንደዚህ

"ልክ ሐናንያ በኤርምያስ አንገት ላይ ያለውን ቀንበር እንዳነሳ"

ከእያንዳንዱ ህዝብ አንገት በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር የተጫነውን ቀንበር እኔ እሰብራለሁ

ሐናንያ በባርነት ውስጥ የሚገኘው ህዝብ እንደ በሬዎች እንደሆነ እና ባቢሎናውያን ህዝቡ ላይ ለከባድ ስራ ቀንበር እንደጫኑበት አድርጎ ይናገራል፡፡ "እኔ መላው ህዝብ ከእንግዲህ የንጉሥ ናቡከደነጾር ባሪያ እንዳይሆን አደርጋለሁ" ወይም "እኔ እያንዳንዱን አገር ከባቢሎን ንጉሥ ከናቡከደነጾር ባርነት ነጻ አወጣለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እያንዳንዱ አገር

"አገር" የሚለው ቃል ለዚያ አገር ህዝብ ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ነው፡፡ "የሁሉም አገር ህዝብ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር የተጫነ ቀንበር

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር የጫነው ቀንበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የተጫነ

በህዝብ ላይ የተደረገ